ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 11
ማንኛውም ሰው በቂ ምግብ፣ ልብስና መኖሪያ ቤትን ጨምሮ ለራሱ እና ለቤተሰቡ በቂ በሆነ የኑሮ ደረጃ የመኖርና የኑሮውን ሁኔታ የማሻሻል መብት አለው።
በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ሲባል
- የይዞታ ባለቤትነት የሕግ ዋስትና መኖር
- የዋጋ ተመጣጣኝነት
- የአገልግሎቶች፣ የጥሬ እቃዎች፣ የመገልገያ ተቋማትና የመሠረተ ልማት አቅርቦት መኖር
- ለኑሮ አመቺነት
- ተደራሽነት እና ሌሎችን በውስጡ ይይዛል::