የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 32(1 እና 2)
- ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመሥረት፣ እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነጻነት አለው።
- ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገሩ የመመለስ መብት አለው።
የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 12(3)
- ብሔራዊ ደኅንነትን፣ የኅብረተሰብ ሰላም፣ የሕዝብን ጤና ወይም ሞራል ወይም የሌሎችን መብቶችና ነጻነቶች ለመጠበቅ ሲባል በዚህ ቃል ኪዳን ከሰፈሩት ድንጋጌዎች ጋር በሚስማማ አኳኋን በሚወጣ ሕግ መሠረት ካልሆነ በስተቀር ከላይ በተጠቀሰው መብት ላይ ምንም ዐይነት ገደብ አይደረግም፡፡