- ብሬል በትምህርት፣ ሐሳብን የመያዝና የመግለጽ ነጻነት፣ የመረጃ ተደራሽነት እንዲሁም በማኅበራዊ አካታችነት ለዐይነ ስውራን ወሳኝ የሆነ የተግባቦት መንገድ ነው።
ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት አንቀጽ 24(3)(ሀ) እና አንቀጽ 9(2)(መ)
አባል ሀገራት፦
- (ዐይነ ስውራን) የሕይወትና የማኅበራዊ እድገት ክህሎት እንዲማሩ፣ ብሎም እንደ ማኅበረሰብ አባልነታቸው በትምህርት የተሟላና እኩል ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል የብሬል ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ፤
- በሕንጻዎችና ለሕዝብ ክፍት በሆኑ ሌሎች መገልገያዎች የመረጃና የአቅጣጫ ምልክቶችን በብሬል እና በቀላሉ ለማንበብና ለመረዳት በሚያስችል ሁኔታ ለመግለጽ ተገቢ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው፡፡