የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር፣ አንቀጽ 7(1)
ማንም ሰው በደሉ እንዲሰማለት የማድረግ መብት አለው፤ ይህም ጸንተው በሚገኙ ስምምነቶች፣ ሕጎች፣ ደንቦችና ልማዶች ዕውቅና ያገኙና ዋስትና የተሰጣቸው መሠረታዊ መብቶቹን የሚጥሱ ድርጊቶች ሲፈጸሙበት ሥልጣን ላላቸው ብሔራዊ አካላት አቤቱታ የማቅረብ መብትን ያካትታል፡፡
- ኢሰመኮ ጸንተው በሚገኙ ሕጎች፣ ደንቦች፣ ስምምነቶችና ልማዶች ዕውቅና ያገኙና ዋስትና የተሰጣቸው መሠረታዊ የሰዎችን የሰብአዊ መብቶች የሚጥሱ ድርጊቶች ሲፈጸሙ አቤቱታዎችን ተቀብለው ከሚመረምሩ ተቋማት መሃከል ይገኛል፡፡