ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 1
- ሁሉም የሰው ልጆች እኩል ክብርና መብቶች ይዘው ነጻ ሆነው ተፈጥረዋል።
ሁሉንም ዐይነት አድሎአዊ የዘር ልዩነቶች ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት፣ አንቀጽ 1 (1) እና 5
- “አድሎአዊ የዘር ልዩነት” ማለት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በባህላዊ ወይም በሌላ በማንኛውም ሕዝባዊ የሕይወት መስክ የሰብአዊ መብቶችን እና የመሠረታዊ ነጻነቶችን እኩል ዕውቅና፣ ተጠቃሚነት ወይም ትግበራ ዋጋ የማሳጣት ወይም የመጉዳት ዐላማ ወይም ውጤት ያለው በዘር፣ በቀለም፣ በትውልድ ወይም በብሔር ወይም በዘር ሐረግ ላይ የተመሠረተ ልዩነት ማድረግ፣ ማግለል፣ መገደብ ወይም ማበላለጥ ነው።
- አባል ሀገራት ሁሉንም ዐይነት የዘር አድልዎ የመከልከል እና የማስወገድ እንዲሁም ማንኛውም ሰው በዘር፣ በቀለም፣ በብሔር ወይም በዘር ሐረግ ልዩነት ሳይደረግበት በሕግ ፊት እኩል የመሆን መብቱን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው።