የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 27(1)
- ማንኛውም ሰው የማሰብ፣ የኅሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው። ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፤ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመግለጽ፣ የመከተል፣ የመተግበር እና የማስተማር መብትን ያካትታል።
የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 18(3)
- የራስን ሃይማኖት ወይም እምነት የመግለጽ ነጻነት ሊገደብ የሚችለው በሕግ በተደነገገው መሠረትና የሕዝብን ደኅንነት፣ ጸጥታ፣ ጤና ወይም ሞራል ወይም የሌሎችን መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ለማስከበር አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ነው።