የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 3 (1) እና (2)
- በመንግሥታዊም ሆነ በግል የማኅበራዊ ደኅንነት ተቋማት፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዳደር ባለሥልጣኖች ወይም በሕግ አውጪ አካላት በሚወሰዱ ማናቸውም ሕፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች የሕፃናት ደኅንነትና ጥቅም በቀዳሚነት መታሰብ አለበት።
- አባል ሀገራት ለሕፃኑ ደኅንነት አስፈላጊ የሆነውን ጥበቃ እና እንክብካቤ ለማረጋገጥ የሕፃኑን ወላጆች፣ ሕጋዊ አሳዳጊዎች ወይም ሌሎች በሕግ ኃላፊነት የተጣለባቸውን ግለሰቦች መብቶች እና ግዴታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ሁሉንም ተገቢ የሕግ ማውጣትና የአስተዳደር እርምጃዎች ይወስዳሉ።