ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 26
- ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው፡፡ ቢያንስ የአንደኛ ደረጃና መሠረታዊ ትምህርት በነጻ ሊሰጥ ይገባል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ግዴታ ሊሆን ይገባል።
- ትምህርት ለሰው ልጅ የተሟላ የስብእና እድገትን ለማምጣት እና የሰብአዊ መብቶችንና መሠረታዊ ነጻነቶች መከበርን ለማጠናከር ያለመ መሆን አለበት፡፡ ትምህርት በሁሉም ሀገራት፣ በተለያዩ ዘሮችና ሃይማኖቶች መካከል መግባባትን፣መቻቻልን እና ወዳጅነትን ሊያጎለብት ይገባል።