ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 26 

  • ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው፡፡ ቢያንስ የአንደኛ ደረጃና መሠረታዊ ትምህርት በነጻ ሊሰጥ ይገባል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ግዴታ ሊሆን ይገባል።  
  • ትምህርት ለሰው ልጅ የተሟላ የስብእና እድገትን ለማምጣት እና የሰብአዊ መብቶችንና መሠረታዊ ነጻነቶች መከበርን ለማጠናከር ያለመ መሆን አለበት፡፡ ትምህርት በሁሉም ሀገራት፣ በተለያዩ ዘሮችና ሃይማኖቶች መካከል መግባባትን፣ መቻቻልን እና ወዳጅነትን ሊያጎለብት ይገባል።