ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል፣ በቂ የኑሮ ደረጃ እና ሰብአዊ መብቶች
“መንግሥት የሠራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደህንነነትና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር አለበት” (አንቀጽ 89 ( 8 ) ኢ.ፊ.ድ.ሪ. ሕገ መንግሥት)
የመሥራት መብት፣ ፍትሐዊና ምቹ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት፤ እንዲሁም የሠራተኛ ማኅበራት መብቶች ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ላይ የተጠበቁ ናቸው።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥትም ከመሥራት መብት በተጨማሪ በሥራ ቦታ ማኅበራትን የማቋቋም መብትንና የሴቶች ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ የማግኘት መብትን ጨምሮ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን ለመወሰን አስፈላጊ የሆኑ መብቶችን እውቅና ይሰጣል፡፡ መንግሥት ሁሉም ሰዎች ኢኮኖሚያዊ ሁኔታቸውን ለማሻሻል እኩል እድል እንዲኖራቸው ለማድረግና ሃብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈልበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴታ አለበት፡፡
Photo credit: Ninara