የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 41 (7) እና 89 (8)
- መንግሥት ዜጎች ጠቃሚ ሥራ የማግኘት ዕድላቸው እየሰፋ እንዲሄድ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳል።
- መንግሥት የሠራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደኅንነትና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር አለበት።
የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባሕል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 7 (ሀ)
- የዚህ ቃል ኪዳን ተዋዋይ ሀገራት እያንዳንዱ ሰው ፍትሐዊና ምቹ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት እንዳለው ዕውቅና ይሰጣሉ። ይህ መብት ቢያንስ፦
- ተገቢ ደመወዝ እና ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ ማግኘትን፣
- ሠራተኛውንም ሆነ ቤተሰቦቹን በጥሩ ሁኔታ ለማኖር የሚያስችል ክፍያ ማግኘትን ያካትታል።