የማሠቃየት እና ሌሎች የጭካኔ፣ ኢ-ሰብአዊ የሆነና ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት ለማስቀረት የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 14

  • እያንዳንዱ አባል ሀገር በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የማሠቃየት ተግባር ሰለባ የሆነ ሰው መፍትሔ እንደሚያገኝ እንዲሁም በተቻለ መጠን የተሟላ ማገገሚያን ጨምሮ ተፈጻሚነት ያለው ፍትሐዊና በቂ ካሳ የማግኘት መብት እንዳለው ማረጋገጥ አለበት።
  • ተጎጂው በደረሰበት የማሠቃየት ተግባር ምክንያት የሞተ እንደሆነ በእርሱ ኃላፊነት እና ድጋፍ ይተዳደሩ የነበሩ ሰዎች ካሳ ሊያገኙ ይገባል።