የኢኮኖሚ ፤ የማኅበራዊ እና የባሕል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፤ አንቀጽ 8
የዚህ ቃል ኪዳን ተዋዋይ ሀገራት ማንኛውም ሠራተኛ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ የሠራተኛ ማኅበራትን ለማቋቋምና የሚመለከተው ማኅበር ደንቦች እስከፈቀዱ ድረስ የመረጠው ማኅበር አባል የመሆን መብቱን ለማረጋገጥ ተስማምተዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 42
ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀኖች፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ሴት ሠራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡