የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማረጋገጥ ማለት በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ሴቶች ያለ ምንም ልዩነት ከወንዶች እኩል ሃሳብ ከማበርከትና ከመደመጥ እስከ ውሳኔ መስጠት ድረስ ትርጉም ባለው መልኩ እንዲሳተፉ ማድረግ ማለት ነው። (በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገው ዓለም አቀፍ ስምምነት- CEDAW)
እንዲሁም የአፍሪካ የሰብአዊና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (Maputo Protocol, እ.ኤ.አ. 2003) አንቀፅ 9 ሀገራት አካታች የሆነ የአስተዳደር ሥርዓት የመገንባት እና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥ አዎንታዊ የሆኑ የሕግ እና ሌሎች እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስገድዳል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 35 ሴቶች በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግስት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ከወንዶች እኩል ተወዳዳሪ እና ተሳታፊ እንዲሆኑ የማስቻል ግዴታን በመንግሥት ላይ ይጥላል።
የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለተሻለ ዓለም!
Photo credit: UNICEF Ethiopia/2017/Demissew Bizuwerk