የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 12(2)
አባል ሀገራት ከታች የተዘረዘሩትን የተወሰኑ አዎንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው፦
- በሴቶች መካከል ማንበብና መጻፍን/ ማስፋፋት፣
- በሁሉም ደረጃዎችና በሁሉም የትምህርት ዘርፎች በተለይም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ትምህርትና ስልጠናዎችን ለሴቶች ማስፋፋት፣
- የሴት ልጆች በትምህርት ቤቶችና በሌሎች ማሰልጠኛ ተቋማት ቅበላና ማቆያን ማበረታታ እንዲሁም ትምህርታቸውን ያለጊዜው ላቋረጡ ሴቶች ሌሎች መርኃ-ግብሮችን ማዘጋጀት አለባቸው።
በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 10
- አባል ሀገራት ሴቶች በትምህርት መስክ ከወንዶች እኩል ያላቸውን መብቶች ለማረጋገጥ በሴቶች ላይ የሚደረጉ አድሎዊ ልዩነቶችን ለማስወገድ ተገቢ የሆኑ እርምጃዎችን ሁሉ መውስድ አለባቸው።