የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 9(3)
- በወንጀል ክስ የተያዘ ወይም የታሰረ ሰው ተገቢ በሆነ ጊዜ ውስጥ ዳኝነት የማግኘት ወይም የመለቀቅ መብት አለው፡፡
- የፍርድ ሂደትን የሚጠባበቁ ሰዎችን በእስር ማቆየት እንደመደበኛ አፈጻጸም ሊታይ አይገባውም፡፡
በአፍሪካ ውስጥ በመያዝ ወቅት፣ በፖሊስ ጥበቃ ስር በማቆየት እና በቅድመ ክስ እስር የማቆያ ቦታዎች ስለሚኖር የአያያዝ ሁኔታ የወጣ መመሪያ፣ አንቀጽ 4(ሀ)
- የቅድመ-ክስ እስር ትዕዛዞች በጥብቅ ሕጉን ተከትለው መከናወን ያለባቸው ሲሆን፤ ማንኛውንም ዓይነት መድሎ መነሻ በማድረግ መሰጠት የለባቸውም።