በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰንዳይ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ማዕቀፍ (እ.ኤ.አ. 2015-2030):-
የሰንዳይ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ማዕቀፍ (እ.ኤ.አ. 2015-2030) በ187 አባል ሀገራት በ3ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ጉበኤ እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን በ2015 ጸድቋል። ይህ ማዕቀፍ መንግሥታት በቀዳሚነት የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ላይ ማተኮር እንዳለባቸው በመግለጽ፣ ኃላፊነቱ በዋነኛነት መንግሥት ላይ የሚወድቅ ቢሆንም ሁሉም ማኅበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ሥራዎች ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው ያስረዳል፡፡
ማዕቀፉ መመሪያ መርሖችን ከማስቀመጡ በተጨማሪ ሀገራት ሊከሰቱ የሚችሉ የአደጋ ሥጋቶችን መቀነስ፤ አዳዲስ ሥጋቶች እንዳይከሰቱ መከላከል፣ አስቀድመው የነበሩ ሥጋቶችን መቀነስ፣ አደጋን የመቋቋም ዐቅምን ማጠናከር እና ተጎጂዎችን ማቋቋም ላይ አጽንዖት ሰጥተው መሥራት እንዳለባቸው ይገልጻል፡፡