የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 27
በጎሳ፣ በሃይማኖት ወይም በቋንቋ ኅዳጣን ባሉበት ሀገር ውስጥ የእነዚህ አባል የሆኑ ግለሰቦች በጋራ ባህላቸውን እንዳያከብሩ፣ ሃይማኖታቸውን እንዳያስፋፉ፣ በቋንቋቸው እንዳይጠቀሙ መብታቸው ሊገፈፍ አይገባም፡፡
የተ.መ.ድ. የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መመሪያ መርሖች፣ መርሕ 9
ሀገራት በተለይም ቀድምት ነዋሪዎችን፣ ኅዳጣንን፣ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ሌሎች ከመሬታቸው ጋር ልዩ ቁርኝት ያላቸውን ሰዎች ከመፈናቀል የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው።