የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 9 (1) (4)፣ 10 (1)
- ማንኛውም ሰው በዘፈቀደ ሊያዝ ወይም ሊታሰር አይችልም። ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ምክንያትና ሥርዓት ውጭ ነጻነቱን አይነፈግም፡፡
- በመያዙ ወይም በመታሰሩ ምክንያት ነጻነቱን የተነፈገ ማንኛውም ሰው ፍርድ ቤቱ ሳይዘገይ ስለእስራቱ ሕጋዊነት እንዲወስንለትና ያለአግባብ መታሰሩን ካረጋገጠም በነጻ እንዲለቀቅ እንዲያዝለት ጉዳዩን ለፍርድ ቤት የማቅረብ መብት አለው፡፡
- ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ አያያዝ ሊደረግላቸውና በተፈጥሮ የተጎናጸፉት ሰብአዊ ክብር ሊጠበቅላቸው ይገባል፡፡