ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 21((ሀ)(ሐ)(መ))
አባል ሀገራት አካል ጉዳተኞች በመረጧቸው የመገናኛ ዘዴ ዐይነቶች ሁሉ መረጃን የመፈለግ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት ነጻነትን ጨምሮ ከሌሎች ጋር በእኩልነት ሐሳብን በነጻነት የመያዝ እና የመግለጽ መብቶቻቸውን መጠቀም እንዲችሉ ተገቢውን ሁሉ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል። ይህም:-
- ለተለያዩ የአካል ጉዳት ዐይነቶች አግባብነት ባላቸው ተደራሽ አቀራረቦች እና ቴክኖሎጂዎች ለጠቅላለው ሕዝብ የታሰበ መረጃን ለአካል ጉዳተኞች በወቅቱ እና ያለተጨማሪ ወጪ መስጠት፤
- በይነመረብን ጨምሮ ለጠቅላለው ሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የግል ተቋም እና አካላት መረጃ እና አገልግሎትን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እና ጥቅም ላይ በሚውሉ ቅርጾች እንዲያቀርቡ ማሳሰብ፤
- በበይነመረብ በኩል መረጃ አቅራቢዎችን ጨምሮ የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎቶቻቸውን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲያደርጉ ማበረታታትን ያካትታል፡፡