ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት አንቀጽ 29 (ሀ) 

  • አባል ሀገራት ለአካል ጉዳተኞች የፖለቲካ መብቶችን እና በእነዚህ መብቶች ከሌሎች ጋር በእኩልነት የመጠቀም ዕድልን ያረጋግጣሉ። እንዲሁም የመምረጥና የመመረጥ መብትና ዕድልን ጨምሮ አካል ጉዳተኞች በቀጥታ ወይም በነጻነት በተመረጡ ተወካዮች አማካኝነት በፖለቲካና በሕዝባዊ ሕይወት ውስጥ ከሌሎች ጋር በእኩልነት ውጤታማ እና የተሟላ ተሳትፎ ማድረግ መቻላቸውን ያረጋግጣሉ።