የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 26
- አባል ሀገራት የእርስ በርስ ድጋፍን በመጠቀም ጭምር አካል ጉዳተኞች የላቀ ነጻነት፣ የተሟላ አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ማኅበራዊና ሞያዊ ችሎታ እንዲሁም በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ውስጥ የተሟላ ተካታችነትና ተሳትፎ እንዲኖራቸው እና ይህንንም አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ውጤታማና ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። ለዚህም አባል ሀገራት በተለይም በጤና፣ በሥራ ስምሪት፣ በትምህርትና በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፎች ሁሉን አቀፍ የማቋቋምና የተኃድሶ አገልግሎቶችንና መርኃ ግብሮችን ማደራጀት፣ ማጠናከር እንዲሁም ማስፋፋት አለባቸው።