የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 44
- ሁሉም ሰዎች ንጹሕና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው።
- መንግሥት በሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች ምክንያት የተፈናቀሉ ወይም ኑሯቸው የተነካባቸው ሰዎች ሁሉ በመንግሥት በቂ እርዳታ ወደ ሌላ አካባቢ መዘዋወርን ጨምሮ ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ወይም ሌላ አማራጭ ማካካሻ የማግኘት መብት አላቸው።
ሁሉም ሰዎች ንጹሕና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 44