ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 7
- ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ ያለምንም ልዩነት እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ይህንን መግለጫ በመፃረር የሚደረግ ልዩነት እና ለልዩነት የሚያነሳሳ ተግባር እንዳይፈጸምባቸው እኩል የሕግ ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 25
- በዘር፣ በብሔር፣ ብሔረሰብ፣ በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲክ፣ በማኀበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው።