የአፍሪካ የወጣቶች ቻርተር፣ አንቀጽ 16 (1) እና 2(ሀ)

  • ማንኛውም ወጣት ሊደረስበት የሚችለውን ከፍተኛውን የአካል፣ የአእምሮ እና የመንፈሳዊ ጤና ደረጃ የማግኘት መብት አለው።
  • አባል ሀገራት የዚህን መብት ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ መሥራት እና በተለይም በገጠር እና ድህነት ባለባቸው የከተማ አካባቢዎች የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎቶች ማሳደግ ላይ ትኩረት በማድረግ ፍትሐዊ እና ዝግጁ የሆነ የሕክምና ድጋፍ እና የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው።