የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 12 (1) እና (2)(መ)
- አባል ሀገራት የማንኛውንም ሰው ሊደረስበት የሚችለውን ከፍተኛውን የአካል እና የአእምሮ ጤና ደረጃ የማግኘት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ።
- የዚህን መብት ሙሉ ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ አባል ሀገራት የሚወስዷቸው እርምጃዎች በሕመም ጊዜ ሁሉንም የሕክምና አገልግሎት እና ክትትል አቅርቦት መኖሩን የሚያረጋግጡ ሁኔታዎችን መፍጠርን ይጨምራል።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 41(4)
- መንግሥት የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሀብት ይመድባል።