የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባሕላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 7(ሀ)
ማንኛውም ሰው ፍትሐዊ እና አመቺ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት አለው፡፡
የዚህ ቃል ኪዳን አባል ሀገራት፦
- ሁሉም ሠራተኞች የሚሰጥ ክፍያ ቢያንስ ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ እኩል ዋጋ ላለው ሥራ ተገቢ እና እኩል እንዲሁም ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን በደኅና ሁኔታ ለማኖር የሚያስችል ክፍያ የሚያገኙ መሆኑን፤
- ሴቶች ወንዶች ከሚሠሩበት ባላነሰ የሥራ ሁኔታ ውስጥ መሥራታቸውንና ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ የማግኘት መብት ያላቸው መሆኑን ተቀብለዋል፡፡