- Version
- Download 32
- File Size 44.00 KB
- File Count 1
- Create Date February 28, 2024
- Last Updated April 9, 2024
በኦሮሚያ ክልል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ የተደረገ የምርመራ ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በኦሮሚያ ክልል በተለይም ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት ሁለት ዓመታት ያደረገውን ክትትል እና ምርመራ መሠረት በማድረግ ከሕግ/ከፍርድ ውጪ የሆኑ እና በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ መሆናቸውን በማመላከት በተለይም የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጡ ጥሪ አድርጓል።
የሁለቱን ዓመታት ግኝቶች ይፋ የሚያደርገው ይህ ዛሬ ይፋ የሆነው ባለ 11 ገጾች ሪፖርት በክልሉ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋ እና ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች ላይ ያተኮረ ነው። መረጃ እና ማስረጃዎች ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂዎች ቤተሰቦች፣ ከዐይን ምስክሮች፣ ከሕክምና ባለሙያዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአባገዳዎች እና ከመንግሥት አካላት በአጠቃላይ 158 ሰዎችን በማነጋገር የተሰባሰቡ ናቸው።