በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍን አስመልክቶ የተደረገ የአፍሪካ ኅብረት ስምምነት (የካምፓላ ስምምነት)፣ አንቀጽ 10
- ተዋዋይ ሀገራት በተቻለ መጠን በሕዝባዊ ወይም በግል አካላት በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ምክንያት የሚፈጠርን መፈናቀል መከላከል አለባቸው፤
- ተዋዋይ ሀገራት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በፕሮጀክቶቹ ሊፈናቀሉ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ሙሉ መረጃ በመለዋወጥና ምክክር በማድረግ አዋጭ የሆኑ አማራጮችን ማጤናቸውን ያረጋግጣሉ፤
- ተዋዋይ ሀገራት አንድ የቀረበ የልማት ፕሮጀክት ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ግምገማ ያካሂዳሉ፡፡