የአፍሪካ የሰዎች እና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር፣ አንቀጽ 24
- ሁሉም ሕዝብ ለእድገቱ አመቺ የሆነ አጠቃላይ ተስማሚነት ያለው አካባቢ የማግኘት መብት አለው።
የኢትዮጵያ ሕገ–መንግሥት፣ አንቀጽ 44
- ሁሉም ሰዎች ንጹሕና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው።
- መንግሥት በሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች ምክንያት የተፈናቀሉ ወይም ኑሯቸው የተነካባቸው ሰዎች ሁሉ በመንግሥት በቂ እርዳታ ወደሌላ አካባቢ መዘዋወርን ጨምሮ ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ወይም ሌላ አማራጭ ማካካሻ የማግኘት መብት አላቸው።