ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 37 (1) እና (2) 

  • ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው።
  • ይህን ውሳኔ ወይም ፍርድ፦
    • ሀ) ማንኛውም ማኅበር የአባላቱን የጋራ ወይም የግል ጥቅም በመወከል፤
    • ለ) ማንኛውንም ቡድን ወይም ተመሳሳይ ጥቅም ያላቸውን ሰዎች የሚወክል ግለሰብ ወይም የቡድን አባል የመጠየቅ እና የማግኘት መብት አለው።