የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36(1) (መ)
- ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎችን እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው።
ዓለም አቀፉ የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 32(2)(ሀ-ሐ)
ተዋዋይ ሀገራት በተለይ፡-
- ዝቅተኛ የቅጥር ዕድሜን ወይም ዕድሜዎችን ይወስናሉ፤
- የሥራ ሰዓትንና የቅጥር ሁኔታዎችን በተመለከተ ተገቢውን ደንብ ያወጣሉ፤
- ይህ አንቀጽ በሚገባ በሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ተገቢ ቅጣቶችን ወይም ሌሎች ክልከላዎችን ያስቀምጣሉ።