Annual Ethiopia Human Rights Situation Report (June 2024 – June 2025)

Annual Ethiopia Human Rights Situation Report

ከሰኔ 2016 እስከ ሰኔ 2017

የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት

related documents

ተዛማጅ ሰነዶች

ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውና ለአራተኛ በጀት ዓመት በዚህ መልኩ ተጠናቅሮ ይፋ የተደረገው ይህ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዓመታዊ ሪፖርት ኮሚሽኑ ባደራጃቸው ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እና የከተማ ጽሕፈት ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ጠቅለል ባለ መልኩ የሚዳስስ ነው።

Comprehensive Sections of the Annual Human Rights Situation Report

የሪፖርቱ ምዕራፎች በተናጠል

“በሪፖርቱ በተሸፈነው ጊዜ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ በርካታ አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች ለመከሰታቸው እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋና ምክንያት የሆነውን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ የትጥቅ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረሶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት ብቸኛው አማራጭ ነው።”

Human rights overview (2024 – 2025)

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውን 4ተኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ባለ 152 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ በበጀት ዓመቱ በተሰበሰቡ መረጃ እና ማስረጃዎች መሠረት ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ጠቅለል ባለ መልኩ የሚያሳይ ሲሆን፤ መልካም እመርታዎች፣ አሳሳቢ ጉዳዮች፣ ምክረ ሐሳቦች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችንም በዝርዝር አካቷል።

Previous Annual Human Rights Situation Reports

ያለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቶች