ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 19 

  • ማንኛውም ሰው በነጻነት የመሰለውን አመለካከት የመያዝ እና ሐሳቡን የመግለጽ መብት አለው፤ ይህ መብት ያለጣልቃ ገብነት አመለካከት የመያዝ እና በሀገራት ድንበር ሳይወሰኑ በማናቸውም ዐይነት የመገናኛ ዘዴዎች መረጃዎችና ሐሳቦችን የማፈላለግ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት ነጻነትን ይጨምራል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ውሳኔ 44/12፤ “የአመለካከት እና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት”፣ አንቀጽ 7 

  • ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ የአመለካከት እና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ጨምሮ ሰብአዊ መብቶችን በማክበር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ መረጃን በማፈላለግ፣ በመቀበል እና በማሰራጨት ነጻነት ላይ አላግባብ የሚጣሉ ገደቦች የመንግሥት ባለሥልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ እና ሙስናን ለማጋለጥ የሚደረጉ ጥረቶችን በማስቀረት ዴሞክራሲን እና የሕግ የበላይነትን ያዳክማሉ።