- Version
- Download 4
- File Size 1.94 MB
- File Count 1
- Create Date August 13, 2025
- Last Updated December 16, 2025
የ 2016 ዓ.ም. የተጠቃለለ የፖሊስ ጣቢያዎች ክትትል ሪፖርት
ይህ ዓመታዊ የክትትል ሪፖርት በ2016 በጀት ዓመት በፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን የሰብአዊ መብቶች አያያዝና ጥበቃ በተመለከተ አበረታች እመርታዎች፣ መንግሥት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮች፣ ማጠቃለያ እና ዝርዝር ምክረ ሐሳቦችን ይዟል። በክትትሉ የተሸፈኑት በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ በጋምቤላ፣ በሐረሬ፣ በኦሮሚያ፣በሲዳማ፣በሶማሊ፣ በደቡብ ኢትዮጰያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባና በድሬደዋ ከተማ አስተዳድሮች የሚገኙ የተመረጡ 346 ፖሊስ ጣቢያዎች እና ይፋዊ ያልሆኑ ጊዜያዊ ማቆያ ቦታዎች ናቸው። ሪፖርቱ ኢሰመኮ በበጀት ዓመቱ በተለያየ ጊዜ የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ባከናወናቸው ክትትል የተገኙ መረጃዎችን እና ማስረጃዎችን አግባብነት ካላቸው ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችና መስፈርቶች እንዲሁም ብሔራዊ ሕጎችና የፖሊሲ ማዕቀፎች አንጻር በመተንተን የተዘጋጀ ነው።
