Areas of Work


የሰብአዊ መብቶች ትምህርት

የሰብአዊ መብቶች ትምህርት ፕሮግራም በመብት ባለቤቶች እና ባለግዴታዎች ዘንድ የሰብአዊ መብቶች ባሕልን ማዳበር፤ እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች እውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከትን ለማጎልበት ያለመ ነው።

ውጤታማ፣ ሥራአታዊ እና ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት ፕሮግራም ስልጠናዎችን፣ ሴሚናሮችን፣ የማስተዋወቅ እንቅስቃሴዎችን እና የሰብአዊ መብቶች ትምህርትን በሀገራዊ የትምህርት ፖሊሲ እና ካሪኩልም ውስጥ እንዲካተት የሚያስችል ውትወታን ያካትታል። ተሳታፊዎችን ማእከል ያደረገ ተግባር ተኮር የስልጠና ዐይነቶችን እንዲሁም የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ለስልጠና የሚያስፈልጉ አዳዲስ ወጤታማ የአቀራረብ ዘዴዎችን መጠቀም፤ የሰብአዊ መብቶች ባህል በኢትዮጵያ እንዲጎለብት ብሎም የሚፈለጉትን የአመለካከት እና የባህሪ ለውጦችን ለማምጣት ይረዳል።


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ዘንድ ስለ ሰብአዊ መብቶች ጥልቅ ግንዛቤ መፍጠርን ዓላማ ያደረገ ሀገራዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር ያዘጋጃል። ውድድሩ የተሳታፊ ተማሪዎችን የሰብአዊ መብቶች ሕጎች እና መርሖች እውቀት፣ አመለካከት እና ክህሎት ለማሳደግ እንደመሰባሰቢያ መድረክ ሆኖ ያገለግላል። በመደበኛ የችሎት ሥርዓት መልክ የሚዋቀረው ሀገራዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች የምስለ ችሎት ውድድር ምናባዊ በሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮችን ከተገቢ ሕጎች አንጻር እንዲመረምሩ እና እንዲሞግቱ ልዩ እድል ይፈጥራል።


ስልጠና:- ወጣቶች፣ ሰብአዊ መብቶች እና የሽግግር ፍትሕ

በዚህ የበይነ መረብ ትምህርት ስለሰብአዊ መብቶች መሠረታዊ ፅንሰ ሐሳብ፣ ስለሽግግር ፍትሕ ምንነት፣ አስፈላጊነት/ግቦች፤ በሽግግር ፍትሕ እና በሰብአዊ መብቶች መካከል ስላለው ቁርኝት እንዲሁም ቀደም ሲል ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፍትሔ ለመስጠት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እንዲችሉ የሚያግዟቸውን ክህሎቶች ትማራላችሁ፡፡