የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ 2017 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውን 5ተኛውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ይፋ አደረገ።

ሪፖርቱ ኮሚሽኑ በሪፖርት ዘመኑ ባካሄደው የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ባሰባሰበው መረጃና ማስረጃ ላይ የተመሠረተ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ የተመዘገቡ አዎንታዊ እመርታዎችንና አሳሳቢነታቸው የቀጠሉ ጉዳዮችን ከምክረ ሐሳቦች ጋር ያመላክታል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፣ ሪፓርቱን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።