የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከፍተኛ አመራሮች በምክትል ሰብሳቢ መላኒ ናገን የተመራ የሞሪሸየስ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ልዑክ ጋር ውይይት አድርገዋል።


ከልዑኩ ጋር በሰብአዊ መብቶች አጠቃላይ ሁኔታ እና የጋራ ትብብር አቅጣጫዎች ዙሪያ የተወያዩት በኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ትምህርትና ጥናት ኮሚሽነር በዳሳ ለሚሳ እንዲሁም የሴቶችና ህጻናት መብቶች ኮሚሽነር አሸነፈች አበበ ናቸው።
በውይይቱ ለሞሪሽየስ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ልዑክ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ወቅታዊ የትኩረት አቅጣጫዎችና ዋና ዋና ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል።


በ5 ዓመቱ የስራቴጅክ ዕቅድ እየተተገበሩ ያሉ ወሳኝ የሰብአዊ መብት ስራዎችም በስፋት ተብራርተዋል።
ሁለቱ ተቋማት በሰብአዊ መብት ጥበቃ፣ ክትትል እና በጋራ መስራት በሚችሉባቸው አዳዲስ የትብብር መስኮች ላይ መክረዋል።


ይህ የልምድ ልውውጥና ውይይት የሁለቱን ሀገራት የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ግንኙነትና የትብብር ማዕቀፍ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።