መድሏዊ አሠራርን በማስወገድ አካታች የሥራ ቦታን መፍጠር የአካል ጉዳተኞችን የመሥራት መብት ለማክበርና ለማስከበር ያለው አስተዋጽዖ የጎላ ነው
ይኸ ጥረት ከትምህርት ሚኒስቴር "በጎ ምላሽ" እንዳገኘ የገለጹት ኮሚሽነሩ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው ሲቪክ ትምህርት "የሰብዓዊ መብቶች መርኆዎችን የሚጣረሱ አስተሳሰቦች" እንደተገኙበት ተናግረዋል
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ እና የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ ለማዳበር ሰፊ ተደራሽነት ያለውን የፊልም ጥበብን በመጠቀም በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ፊልሞች ለእይታ እና ለውይይት ይቀርባሉ
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በግጭቶች እና በጥቃቶች እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ የአካል ጉዳቶች እና መፈናቀሎች እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሆኑ በርካታ አመላካቾች እንዳሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
The festival takes place in Adama, Addis Ababa, Bahir Dar, Hawassa & Jigjiga
በኢትዮጵያ በህይወት የመኖር መብት በከፋ አደጋ ውስጥ መውደቁንም ተቋሙ ገልጿል
“በኦሮምያ ክልል በሲቪሎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ፣ የአካል ጉዳትና መፈናቀል የፌዴራል መንግሥቱን አፋጣኝ እርምጃና ተጨባጭ ዘላቂ መፍትኄ የሚሻ ነው” ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳስቧል
በሰላም እና ጸጥታ ዘርፍ፣ በፖሊስ፣ በዓቃቤ ሕግ፣ በፍርድ ቤት እና በማረሚያ ቤቶች የሚከናወኑ ሥራዎች በዋነኝነት የሰብአዊ መብቶችን እውን የሚያደርጉ በመሆናቸው አሠራሮቻቸውን ማሻሻል ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅ እና መሟላት መሰረት ነው
በኦሮሚያ ክልል ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ላይ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች “በአይነታቸው እና በቁጥራቸው” መጨመራቸውን የገለጸው ኢሰመኮ፤ በተለያዩ ወቅቶች፣ የተለያዩ ቡድኖች “ሙሉ ቀበሌዎችን ወይም ወረዳዎችን ጭምር” ተቆጣጥረው እንደቆዩ ጠቁሟል
በክልሉ በሲቪል ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ፣ አካል ጉዳት እና መፈናቀል መጠነ ሰፊ ምርመራን ጨምሮ እየደረሰ ካለው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጋር የሚመጣጠን የፌዴራል መንግሥቱን አፋጣኝ እርምጃ እና ተጨባጭ ዘላቂ መፍትሔ የሚሻ ነው