በታኅሣሥ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ሁሉም ተባባሪ ድርጅቶች በጋራ ጊዮን ሆቴል በሚገኘው ጋርደን ግሩቭ ዎክ መናፈሻ የጋራ ዝግጅት ላይ የዚህን ዓመት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን መሪ-ቃል ዋና መልዕክት በማስተዋወቅ የዝግጅቶቹን መዝጊያ መርኃ ግብር አዘጋጅተዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በኅዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዳማ ኦሊያድ ሲኒማ፣ በኅዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ሌዊ ሲኒማ በመጨረሻም በታኅሣሥ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በጋርደን ግሩቭ ዎክ መናፈሻ ይካሄዳል
ኢሰመኮ በተለይም ከእ.ኤ.አ. ከኅዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሚታሰቡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀናት #ጤናማቃላት ወይም #KeepWordSafe የሚል የማኅበራዊ ድረ ገጽ እንቅስቃሴ “ሃሽታግ” እና ታስበው የሚውሉትን ዓለም አቀፍ ቀናት ማሳወቁ ይታወሳል።