የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከፍሬድሪክ ኤልበርት ስቲፍታንግ (Friedrich Elbert Stiftung) ጋር በመተባበር የንግድ እና የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር ዝግጅት ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል። የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፤ ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት የሰጠ የንግድና የልማት አሠራርን ማስቀጠል ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም የመንግሥት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት መሪዎችና ሌሎችም ቅንጅታዊ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል
ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ነው
የዩናዩትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሃገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ያወጣውን ዓመታዊ ሪፖርት በተመለከተ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከቪኦኤ-አማርኛ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ
የቅድመ ክስ እሥርን ለመቆጣጠር እና ለማስቀረት እንዲሁም የፍትሐዊ እና ሰብአዊ መብቶች መርኾችን ያካተተ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት፤ የፍትሕ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
ዋና ኮሚሽነሩ ይህንን ኃላፊነት ከያዙ አምስት ዓመታት ሞልተው የመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ሊጠናቀቅ ወራት ቀርተዋል፡፡ ሲሳይ ሳህሉ ከዋና ኮሚሽነር ዳንኤል ጋር በተቋሙና በአጠቃላይ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና ምልከታ ላይ ያደረገው ቃለ ምልልስ
ግጭት ባለበት አካባቢ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ዓለም አቀፍ ስልቶችን ጭምር በመጠቀም የማጣራት ሥራ እንደሚሠራ ተናግረዋል
ኢሰመኮ ለሴቶችና ሕፃናት መብት ኮሚሽነርነት፤ በዕድሜ ከ35 በላይ ሆና የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነች፣ የመብት ተቆርቋሪነትና የሙያ ብቃት አላት ብለው የሚያምኗትን ኢትዮጵያዊት እስከ ሚያዚያ 22 መጠቆም እንደሚቻል ገለፀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ካሉት አምስት ኮሚሽነሮች መካከል አንዷ በነበሩት የሴቶች እና ህጻናት መብቶች ዘርፍ ኃላፊ ምትክ፤ አዲስ ኮሚሽነር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሊሾም ነው። ለተተኪ ኮሚሽነርነት ዕጩ የሚሆኑ ግለሰቦች ጥቆማ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እንደሚካሄድም ተገልጿል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በወንጀል ፍትህ ሥርዓት ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ህፃናትን መብቶች አያያዝን በተመለከተ ያደረገውን የክትትል ሪፖርት ይፋ አደረገ
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ በወንጀል ሥነ ሥርዓትና በማስረጃ ደንቦች ባለመካተታቸው፣ የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ፍትሕ እንዳያገኙ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (አሰመኮ) አስታወቀ