የአካል ጉዳተኞችን አመራር ማሳደግ እና የመብቶቻቸውን መከበር ያለመ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ተዘጋጀ
በአዲስ አበባ 90 በመቶ ሕንጻዎች ለአካል ጉዳተኞች አይሆኑም ተብሏል
“ካሉ አካል ጉዳተኛ ሕፃናት ውስጥ ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት የትምህርት እድል እያገኙ አይደለም” - ኢሰመኮ
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚተላለፉ እገዳዎች የሲቪክ ምህዳሩን በማጥበብ በማህበር የመደራጀት መብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳይፈጥሩ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡ ኢሰመኮ፤ ተቋሟቱ የፈጸሟቸውን ከባድ የሕግ ጥሰቶች በዝርዝር ባላስቀመጠ ደብዳቤ መታገዳቸው አሳሳቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ነው ያለው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ፣ በሰብአዊ መብቶች ላይ ትኩረት ያደረገ የፊልም ፌስቲቫል በኢትዮጵያ ከተሞች በማካሄድ ላይ መኾኑን አስታውቋል
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በግዳጅ የመከላከያ ሰራዊት አባል እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ብሏል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን
ኮሚሽኑ ከኅዳር 4 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ እና ሻሸመኔ ከተሞች እንዳካሄደ በገለጸው ክትትል እና ምርመራ፣ "የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ" በሚል ሕፃናትንና የአእምሮ ህሙማንን ጨምሮ የክልሉ ነዋሪዎች በግዳጅ መያዛቸውን አመልክቷል
ኢሰመኮ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት ለመከላከያ ሰራዊት ምልመላ እናካሂዳለን በሚል ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን በግዳጅ እንደያዙ እንዲሁም የተያዙትን ለመልቀቅ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስገደዳቸውን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ወደ ምርመራ ገብቻለሁ ብሏል
ኮሚሽኑ ምርመራውን በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ እጩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማቆያ ስፍራዎችን በመጎብኘት፤ በማቆያ ስፍራዎቹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በጉዳዩ ዙሪያ ቃለ መጠይቅ ማድረጉን ገልጿል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ በሚሸፍነው ሪፖርቱ በክልሉ ሴቶች ጥቃት እንደሚደርስባቸው እንደሚደፈሩም አረጋግጧል