ሁሉም ሰው ለግሉ እና ለቤት ውስጥ አገልግሎት በቂ የሆነ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ተቀባይነት ያለው፣ በአካል ተደራሽ እና በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ ውሃ የማግኘት መብት አለው
The human right to water entitles everyone to sufficient, safe, acceptable, physically accessible and affordable water for personal and domestic uses
አባል ሀገራት ለአካል ጉዳተኞች ትምህርት የማግኘት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ
States Parties recognize the right of persons with disabilities to education
እያንዳንዱ አባል ሀገር በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የማሰቃየት ተግባር ሰለባ የሆነ ሰው መፍትሔ እንደሚያገኝ እንዲሁም በተቻለ መጠን የተሟላ ማገገሚያን ጨምሮ ተፈጻሚነት ያለው ፍትሐዊና በቂ ካሳ የማግኘት መብት እንዳለው ማረጋገጥ አለበት
Each State Party shall ensure in its legal system that the victim of an act of torture obtains redress and has an enforceable right to fair and adequate compensation, including the means for as full rehabilitation as possible
ሁሉም ሕዝብ ለእድገቱ አመቺ የሆነ አጠቃላይ ተስማሚነት ያለው አካባቢ የማግኘት መብት አለው
All people shall have the right to a general satisfactory environment favourable to their development
ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎችን እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው
Every child has the right not to be subjected to exploitative practices, neither to be required nor permitted to perform work which may be hazardous or harmful to his or her education, health or wellbeing