ሴቶች ሠራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው
Women workers have the right to equal pay for equal work
አባል ሀገራት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ በአዲስና ታዳሽ የኃይል ምንጮች እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎች ላይ ምርምርንና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት፣ በዚሁም ላይ የሴቶችን ተደራሽነት እና የቁጥጥር ተሳትፎ ለማመቻቸት ተገቢውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ ይገባቸዋል
States Parties shall take all appropriate measures to promote research and investment in new and renewable energy sources and appropriate technologies, including information technologies and facilitate women’s access to, and participation in their control
ማንኛውም ሰው የማሰብ፣ የኅሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው
Everyone has the right to freedom of thought, conscience and religion
ማንኛውም ሰው የትምህርት መብት አለው
Everyone has the right to education
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሠረተ ልዩነት ሳይደረግበት በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥ እና የመመረጥ መብት አለው
Every Ethiopian national, without any discrimination based on colour, race, nation, nationality, sex, language, religion, political or other opinion or other status, has the right to vote and to be elected at periodic elections to any office at any level of government