Every individual shall have the right to have his cause heard
ማንም ሰው በደሉ እንዲሰማለት የማድረግ መብት አለው
ወጣት አጥፊዎች በማረሚያ ወይም በመቋቋሚያ ተቋሞች ከአዋቂዎች ተለይተው መያዝ አለባቸው
Juvenile offenders admitted to corrective or rehabilitative institutions shall be kept separate from adults
All persons have the right to a clean and healthy environment
ሁሉም ሰዎች ንጹሕና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው
Every individual shall have the right to the respect of the dignity inherent in a human being and to recognition of his legal status
ማንኛውም ግለሰብ ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰው ልጅ ክብር የማግኘት እና በሕግ ፊትም ዕውቅና የማግኘት መብት አለው
No one shall be subjected to torture or to cruel, inhuman, or degrading treatment or punishment
ማንም ሰው ለማሰቃየት ተግባር ወይም ጭካኔ ለተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም ክብርን ለሚያዋርድ አያያዝና ቅጣት ሊጋለጥ አይገባም