ቤተሰብ የኅብረተሰብ ተፈጥሯዊ እና መሠረታዊ መነሻ ነው። ከኅብረተሰብና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው
The family is the natural and fundamental unit of society and is entitled to protection by society and the State
Braille is a means of communication, and it is essential in education, freedom of expression and opinion, access to information and social inclusion for those who use it
ብሬል በትምህርት፣ ሐሳብን የመያዝና የመግለጽ ነጻነት፣ የመረጃ ተደራሽነት እንዲሁም በማኅበራዊ አካታችነት ለዐይነ ስውራን ወሳኝ የሆነ የተግባቦት መንገድ ነው
ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው
Trafficking in human beings for whatever purpose is prohibited
መንግሥት የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሀብት ይመድባል
The State has the obligation to allocate ever increasing resources to provide to the public health, education and other social services
የሁሉንም የሰው ዘር አባላት በተፈጥሮ የተገኘ ክብር እንዲሁም እኩል እና የማይገፈፉ መብቶች ዕውቅና መስጠት በዓለም ላይ ለነጻነት፣ ፍትሕ እና ሰላም መሠረት ነው
Recognition of the inherent dignity and of the equal and inalienable rights of all members of the human family is the foundation of freedom, justice and peace in the world