ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ እና የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ ለማዳበር ሰፊ ተደራሽነት ያለውን የፊልም ጥበብን በመጠቀም በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ፊልሞች ለእይታ እና ለውይይት ይቀርባሉ
በክልሉ በሲቪል ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ፣ አካል ጉዳት እና መፈናቀል መጠነ ሰፊ ምርመራን ጨምሮ እየደረሰ ካለው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጋር የሚመጣጠን የፌዴራል መንግሥቱን አፋጣኝ እርምጃ እና ተጨባጭ ዘላቂ መፍትሔ የሚሻ ነው
የተሟላ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ወይም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ እንዲሻሻል ያስፈልጋል
መንግሥት በኮንሶ ዞን እና በአጎራባች ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተደራጀ የምዝገባ ሥርዓት ማከናወን፣ የወሳኝ ኩነት አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ሰነዶችን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ፣ እንዲሁም በክልሉ ለተደጋጋሚ መፈናቀል መንስዔ ለሆኑ ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያፈላልግ ይገባል
የኮቪድ ወረርሽኝ፣ ድርቅ፣ ጦርነትና ግጭት ሳቢያ በሴቶችና ሕፃናት መሰረታዊ መብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደራቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል
በካምፓላ ስምምነት ውስጥ የተካተቱ እና እንደ የሰነድና ምዝገባ፣ የጸጥታና ደኅንነት፣ የመንቀሳቀስ ነጻነት እና ፍትሕ የማግኘት መብት የመሳሰሉ መብቶችን እና በመንግሥት ላይ የተጣሉ ግዴታዎች ዙሪያ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ማሻሻል ይገባል
ከሰኔ 7 እስከ ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጎጂዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች...
በድርጊቱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂ ቡድን፣ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂ ቡድን፣ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይሎች፣ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች እና ተባባሪ ወጣቶች ተሳትፈዋል፤ ድርጊቱን ሲመሩ እና ሲያስፈጽሙ የነበሩ ኃላፊዎችም ነበሩ
ሰዎቹ ከሌሎች የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች በተለየ መልኩ ከሕግ አግባብ ውጪ እና የመንቀሳቀስ መብታቸው ተነፍጎ፣ የሰብአዊ ድጋፍ በበቂ ሁኔታ ሳይቀርብላቸው በጃሬ መጠለያ ጣቢያ ለበርካታ ወራት ተይዘው ቆይተዋል
በሲቪል ሰዎች ላይ ለደረሰው ግድያ፣ ጉዳት እና መፈናቀል ተጠያቂነት ሊረጋገጥ፣ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ስምሪትን የተመለከቱ እርምጃዎች የሰዎች ደኅንነት ላይ ስጋት በማያሳድር መልኩ ሊሆን ይገባል