አጭር የፖሊሲ መግለጫ:- በኢትዮጵያ የአረጋውያንን ሰብአዊ መብቶች ለማሳደግ የማኅበራዊ ጥበቃ ሥርዓት ማጠናከሪያ ስትራቴጂ እ.ኤ.አ. በ2023 የወጣው የዓለም ማኅበራዊ ሪፖርት የዓለማችን ሕዝብ ዕድሜ መግፋት ሁኔታ/አዝማሚያ የማይቀለበስ መሆኑን እና ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በሚቀጥሉት ሦስት አስርት ዓመታት ውስጥ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ቁጥር ፈጣን እድገት የሚመዘገብበት መሆኑ እንደሚጠበቅ ይገልጻል (የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች...
This policy brief explores the current social protection landscape in Ethiopia, identifies gaps in service provision, and proposes actionable recommendations to build a more inclusive and resilient system for older persons. አጭር የፖሊሲ መግለጫ:- በኢትዮጵያ የአረጋውያንን ሰብአዊ መብቶች ለማሳደግ የማኅበራዊ ጥበቃ ሥርዓት ማጠናከሪያ ስትራቴጂ
ክትትሉ በዋናነት ያተኮረው በማእከላቱ አደረጃጀት፣ በተጠቃሚዎች ልየታ ሥርዓት፣ በአገልግሎት ዓይነቶች እና በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ሲሆን፤ አግባብነት ካላቸው ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ሕጎች እና መርሆች አንጻር በመገምገም ምክረ ሐሳቦችን ይሰጣል፡፡ በዚህ ክፍል የክትትሉ አንኳር ጉዳዮች እና ምክረ ሐሳቦች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ አረጋውያን ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው ለሚመጡ አድሎዎች እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ በመሆናቸው እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለመስጠት ሲባል አረጋውያንን በአንድ ማእከል ውስጥ አሰባስቦ እንክብካቤ መስጠት...