የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ፤ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ የአካል ጉዳተኞች የከፍተኛ ትምህርት ተካታችነትን ሁኔታ ለመፈተሽ ያስችለው ዘንድ የኢትዮጵያ የሕግ እና የፖሊሲ ማዕቀፎች እንዲሁም አጠቃላይ ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣ የመረጃ እና የአመለካከት ተደራሽነትን...
“ምላሹ ሥሙ ትልቅ ነው፤ ሲደርስ ግን ረኀባችንን የሚያስታግሥ አይደለም’’ … የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ከየካቲት 14 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በድርቁ ጉዳት ደርሶባቸው እና ለናሙና የተመረጡ አካባቢዎችን በመዘዋወር የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በማድረግ ያዘጋጀውንና በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነውን ሪፖርት ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ...
Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) 2021/2022 Activity Report
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዐበይት ክንዋኔዎችና ውጤቶች | 2014 ዓ.ም.
ክትትሉ በዋናነት ያተኮረው በማእከላቱ አደረጃጀት፣ በተጠቃሚዎች ልየታ ሥርዓት፣ በአገልግሎት ዓይነቶች እና በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ሲሆን፤ አግባብነት ካላቸው ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ሕጎች እና መርሆች አንጻር በመገምገም ምክረ ሐሳቦችን ይሰጣል፡፡ በዚህ ክፍል የክትትሉ አንኳር ጉዳዮች እና ምክረ ሐሳቦች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ አረጋውያን ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው ለሚመጡ አድሎዎች እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ በመሆናቸው እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለመስጠት ሲባል አረጋውያንን በአንድ ማእከል ውስጥ አሰባስቦ እንክብካቤ መስጠት...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ሠራተኞች ላይ የተሠሩ ጥናቶችን እና የቀረቡለትን በርካታ ቅሬታዎችን መሰረት በማድረግ ያከናወነውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ባለ 58 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። በክትትል ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሠሩ በተለይም በሃዋሳ፣ ባሕር ዳር፣ አዲስ አበባ እና ጅማ ከተሞች፤ በአጠቃላይ 122 ሠራተኞች (83 ወንድ እና 39 ሴት)፣ 18...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ያለበትን ሁኔታ ለመረዳት፤ የመፈናቀሉ አውድ እና መንስኤዎች፣ በመፈናቀል ወቅት ያጋጠሙ አንኳር የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክፍተቶች እና የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎቶችን ለመለየት ከሐምሌ 24 እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች (ደ/ብ/ብ/ሕ) ክልል በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በዲራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ...
ይህ ዓመታዊ የሴቶችና የሕፃናት መብቶች የዘርፍ ሪፖርት ከመስከረም 2014 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 2014 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን ኢሰመኮ ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው አጠቃላይ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተጨማሪነት በተለይ የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ኮሚሽኑ የለያቸውን አበረታች እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን እና ምክረ-ሃሳቦችን አካቷል፡፡ ኮሚሽኑ...
(Download the English version below) ⬇️ ይህ ዓመታዊ የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ በሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ባለፈው የበጀት ዓመት ኮሚሽኑ ባከናወናቸው ልዩ ልዩ ተግባራት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ...