- Version
- Download 1049
- File Size 235.35 KB
- File Count 1
- Create Date September 28, 2022
- Last Updated October 5, 2022
በጋምቤላ ከተማ በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) ታጣቂዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የተደረገ ምርመራ ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ከተማ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) መካከል የተደረገው ውጊያን ተከትሎ ከሰኔ 7 እስከ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በክልሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ታጣቂ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን፣ የንብረት ጉዳት እና ዘረፋዎችን በተመለከተ ከሰኔ 20 እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ያደረገውን ምርመራ ባለ 13 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል።
በዚህ የምርመራ ሂደት ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከዓይን እማኞች እና ሌሎች ምስክሮች ጋር ቃለ መጠይቅ የተደረገ ሲሆን፤ በአጠቃላይ 58 ሰዎችን (25 ሴቶች እና 33 ወንዶችን) አነጋግሯል። ኮሚሽኑ ከፍትሕ እና የጸጥታ ተቋማት ኃላፊዎች እና ሌሎች የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር ውይይቶች እና ቃለ መጠይቆችን አድርጓል። ለምርመራው ሥራ አግባብነት ያላቸውን የሰነድ፣ የፎቶ ግራፍ፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እና ዲጂታል ማስረጃዎችን ሰብስቧል፤ እንዲሁም የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡